የቀድሞዋ ቤተክርስቲያን መልክ:: ሐዋ.9:31-35 ክፍል 1

የቀድሞዋ ቤተክርስቲያን መልክ:: ሐዋ.9:31-35 ክፍል 1

Voice of Truth and Life

08/07/2021 7:00AM

Episode Synopsis "የቀድሞዋ ቤተክርስቲያን መልክ:: ሐዋ.9:31-35 ክፍል 1"

መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ በወረደ ጊዜና የመጀመሪያውን የወንጌል ምስክርነት አሰምተው ሰዎች በኢየሱስ ባመኑ ጊዜ የቤተክርስቲያን ውበት መገለጥ ጀመረ:: በአመታት መካከል በቁጥር እየበዛችና እያደገች ደግሞም እየተገለጠች መጣች:: መከራ እየጨመረ በመጣ መጠንም በቤተክርስቲያን አብዝቶ ድንቅና ተአምራት ይሆን ነበር:: ፀጋም ይገለጥ ነበር:: በጉዞ ውስጥ ድካም ሲኖር ዝለት ሲመጣ ጌታ ደግሞ ተሃድሶን ያደርጋል:: ጉብኝት ይሆናል:: ሀይል ይታደሳል:: እንደ ቀድሞ የእግዚአብሔር ሀይል ይገለጣል:: በዚህን ጊዜ ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከእርሱ ጋር ያለው የሰው ግንኙነት እንዲታደስ ይፈልጋል::

Listen "የቀድሞዋ ቤተክርስቲያን መልክ:: ሐዋ.9:31-35 ክፍል 1"

More episodes of the podcast Voice of Truth and Life