304 || ኢየሱስን መውደድ! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን

304 || ኢየሱስን መውደድ! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

03/12/2023 9:19PM

Episode Synopsis "304 || ኢየሱስን መውደድ! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን"

"ኢየሱስን መውደድ!" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት። ጌታ ኢየሱስ ሰዎችን ጥያቄ እየጠየቀ ያገለግላቸው ነበር። ማር. 10፡46-51 የጤሜዎስ ልጅ በርጤሜዎስ ተጠየቀ። ቁ. 51 "ምን አደርግልህ ዘንድ ትወዳለህ?" ዮሐ. 5፡1-8 ለ38 አመታት ሽባ የነበረው ሰው ተጠየቀ። ቁ. 6 "ልትድን ትወዳለህን?" ዮሐ. 9፡35-38 ከመወለዱ ጀምሮ ዓይነ ስውር የነበረው ሰውዬ ከቤተ መቅደስ ካስወጡት በኋላ ተጠየቀ። ቁ. 35 "በሰው ልጅ ታምናለህን?" ዮሐ. 21፡14-19 ጴጥሮስ ተጠየቀ፡ - ቁ. 15 "ከእነዚህ አብልጠህ ትወደኛለህን?" ቁ. 16 "በእውነት ትወደኛለህን?" ቁ. 17 "ትወደኛለህን?" ኢየሱስን መውደድ ማለት ምን ማለት ነው? ኢየሱስን መውደድ - ቃሉን መታዘዝ ነው። ዮሐ. 14፡21 ኢየሱስን መውደድ - ለመንፈስ ቅዱስ ድምጽ መታዘዝ ነው። ዮሐ. 14፡7፣ 12-15/ ሮሜ 8፡15 ጴጥሮስ ለጌታ ጥያቄዎች መልስ ከሰጠ በኋላ በህይወቱ የታዩ ለውጦች፡- በጾምና በጸሎት ከሌሎች ወንድሞችና እህቶች ጋር ኅብረት እያደረገ ይተጋ ነበር። ሐዋ. 1 በበዓለ ሐምሳ ቀን መንፈስ ቅዱስን ተሞልቶ ወንጌልን ይሰብክ ነበር። ሐዋ. 2 በመንፈስ ተመርቶ ለአህዛብ ወንጌልን መመስከር ተጓዘ። ሐዋ. 10

Listen "304 || ኢየሱስን መውደድ! || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን"

More episodes of the podcast Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland