131_ጌታ ቅርብ ነው || ክፍል 1 || በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር)

131_ጌታ ቅርብ ነው || ክፍል 1 || በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር)

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

08/11/2020 1:01PM

Episode Synopsis "131_ጌታ ቅርብ ነው || ክፍል 1 || በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር)"

ጌታ ቅርብ ነው  በተከለ ማርቆስ (ዶ/ር) በአባቶች ቀን ፕሮግራም ላይ  በፊሊ 4:6 ላይ የተመሰረተ ከ እ/ር ቃል መልእክት የቀረበ "ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።"ፊሊ 4:4-6 "እናንተም ትጠሩኛለችሁ፥ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፥ እኔም እሰማችኋለሁ።  እናንተ ትሹኛላችሁ፥ በፍጹም ልባችሁም ከሻችሁኝ ታገኙኛላችሁ።"ኤር 29:12-13 "እግዚአብሔርም መልካሙን መዓዛ አሸተተ፤ እግዚአብሔርም በልቡ አለ፦ ምድርን ዳግመኛ ስለ ሰው አልረግምም፥ የሰው ልብ አሳብ ከታናሽነቱ ጀምሮ ክፉ ነውና፤ ደግሞም ከዚህ ቀድሞ እንዳደረግሁት ሕያዋንን ሁሉ እንደ ገና አልመታም።"ዘፍ 8:21 "ኢየሱስ ግን፦ አንድ ሰው ዳስሶኛል፥ ኃይል ከእኔ እንደ ወጣ እኔ አውቃለሁና አለ።  ሴቲቱም እንዳልተሰወረች ባየች ጊዜ እየተንቀጠቀጠች መጥታ በፊቱ ተደፋች፥ በምን ምክንያትም እንደ ዳሰሰችው ፈጥናም እንደ ተፈወሰች በሕዝቡ ሁሉ ፊት አወራች።"ሉቃ 8:46

Listen "131_ጌታ ቅርብ ነው || ክፍል 1 || በወንድም ተከለ ማርቆስ (ዶ/ር)"

More episodes of the podcast Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland