197 || የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት || ክፍል 1 || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን

197 || የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት || ክፍል 1 || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን

Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland

23/01/2022 5:09PM

Episode Synopsis "197 || የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት || ክፍል 1 || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን "

"የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት" በሚል ርዕስ በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን የቀረበ የእግዚአብሔር ቃል መልዕክት የመጀመሪያው ክፍል።  የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል፡ ራዕይ ምዕራፍ 1 ሙሉ ምዕራፍ 1 ውስጥ ልብ ማለት የሚገቡን 7 ነጥቦች፡-  1) የመልዕክቱ ባለቤት፡- እግዚአብሔር ራሱ ነው።  እግዚአብሔር > ኢየሱስ > መልዓክ > ዮሐንስ 2) የመልዕክክት ተቀባይ፦ ዮሐንስ ነው።  3) መልዕክቱን የተቀበለበት ቦታና ሁኔታ፦ ቦታው ፍጥሞ በተባለ ደሴት ሲሆን፣ በእሥር ላይ ሆነ ነበር መልዕቱን የተቀበለው።  4) የመልዕክቱ ዓላማ፦ ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እና የመልዕክቱ ተደራሲያን የሆኑ 7ቱ አቢያተ ክርስቲያናትን ለማንቃት ነው። በተጨማሪም በመጨረሻው ዘመን በዓለም ላይ ሊሆን ያለውን ለማመልከት ነው።  5) ሰባት ቁጥር በመጽሐፉ ውስጥ መደጋገሙ ራሱን የቻለ መልዕክት አለው። በተጨማሪም ብፁዓን የሚለው ቃል ራሱ 7 ጊዜ በራዕይ መጽሐፍ ውስጥ ተደጋግሟል።  6) ኢየሱስ ለሐዋሪያው ዮሐንስ ከዚህ በፊት ባልተለመደ አቀራረብና መንገድ ራሱን ገልጧል። ለምሳሌ መልኩን ለመግለጽ ሐዋሪያው የተጠቀመባቸውን አገላለጾች ልብ ማለት ይቻላል።  7) ጌታ ወደ ዮሐንስ ሲመጣ ዮሐንስ የነበረበት ሁኔታ፦ ስለክርስቶስ መከራን እየተቀበለ ያለበት ሁኔታና በዚያ ችግር ውስጥም ቢሆን በጌታ ቀን በመሆን ከመሆን እንዳላገደው እንመለከታለን። 

Listen "197 || የዮሐንስ ራዕይ ለ7ቱ አቢያተ ክርስቲያናት || ክፍል 1 || በወንጌላዊ ዘገየ መኮንን "

More episodes of the podcast Ethiopian Christian Fellowship Church in Finland