Episode Synopsis "ዮፍታሔ፣ ዮሐንስ እና ዮናስ"
ወንድማማቾቹ ዮሐንስ እና ዮናስ መምህር ፣ ገጣሚ እና አብዮተኞች ነበሩ። በተለያየ ዕርከንም ቢሆን በኢትዮጵያ ተማሪዎች ንቅናቄ ውስጥ ተሳትፎ ነበራቸው። ዮናስ የታላቅ ወንድማቸው ዮሐንስ አድማሱን ጅምር ሥራዎች ማጠናቀቅ በሕይወታቸው ትልቅ ትኩረት የሰጧቸው ጉዳዮች እንደነበሩ የቅርብ ወዳጆቻቸው በተደጋጋሚ ይናገራሉ። የታላቅ ወንድማቸው እስኪ ተጠየቁ የተባለ የግጥም መጽሐፍ ለሕትመት ያበቁት ዮናስ ናቸው። የኃይሌ ገሪማን ጤዛ ፊልም ካፕሽን ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ በመተርጎም አብረዋቸው የሰሩት ሔራን ሰረቀ ብርሃን እንዲያውም "ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ" የተባለውን መጽሐፍ ሲያልቅ የእኔም ጉዞ ያበቃል» ይሉ ንደነበር ለመገናኛ ብዙኃን ተናግረው ነበር። "ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ፤ አጭር የሕይወቱና የጽሑፉ ታሪክ" ለሕትመት በቅቶ በብሔራዊ ቲያትር የተመረቀ ዕለት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ ዳይሬክተር የነበሩት ፕሮፌሰር ማስረሻ ፈጠነ ያሰሙት ንግግር ዮናስ ምን ያክል ተጨናቂ (meticulous) እንደነበሩ የሚጠቁም ነው። ይኸኛው ደግሞ ሐይማኖት አለሙ ሶስቱ ዮዎች በሚል ርዕስ የዮፍታሔ ንጉሤን፣ የዮሐንስ እና ዮናስ አድማሱን የሕይወት ታሪክ አጠር አድርጎ ያቀረበበት ነው። አጭር የሕይወት ታሪክ ሐይማኖት ዓለሙ እንደተረከው