ከሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ኒውክሌር ፡ የኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሌር ኢነርጂ የመገንባት ውጥን

23/09/2025 1h 0min Temporada 1 Episodio 43
ከሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ኒውክሌር ፡ የኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሌር ኢነርጂ የመገንባት ውጥን

Listen "ከሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ወደ ኒውክሌር ፡ የኢትዮጵያ ሰላማዊ የኒውክሌር ኢነርጂ የመገንባት ውጥን"

Episode Synopsis

“ለሀገር ልማትና ምጣኔ ሐብት ዕድገት፣ አስተማማኝ ኢነርጂ በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ስለዚህ፣ ሌሎች ምንጮች ላይ ጥገኛ ያልሆነ፣ የተረጋጋና አስተማማኝ የኢነርጂ የኃይል ምንጭ የሚሆን ፓወር ፕላንት መገንባቱ ጠቃሚ ነው '' ሲሉ የኒውክሌር ሶሳይት ኦፍ ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እምሻው ዳምጠው ተናግረዋል።

የኮይሻ ሀይድሮፓወር ፕሮጀክት ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር አባይነህ ጌትነት በበኩላቸው፡ -
“ኢትዮጵያ አሁን ላይ ቀጠናው ለማስተሳሰር በብርቱ እየሰራች ናት። እስካሁን ሱዳን፣ ጅቡቲ እና ኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል እያስገቡ ነው። ወደ ታንዛንያም ለመላክ የስምምነት እና ሌሎች ተግባራት በመከናወን ላይ ይገኛሉ'' ብለዋል።
ኢትዮጵያ የህዳሴን ግድብ የሚተካከል ለሰላማዊ ዓላማ ብቻ የሚውል የኒውክሌር ፕላንት በቅርቡ ስራ እንደምታስጀምር ከሰሞኑ ይፋ አድርጋለች። የዛሬው የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራምም ይህን መረጃን መሠረት አድርጎ በሰላማዊ የኒውክሌር ኢነርጂ እና የሀይድሮፓወር ፕሮጀክት ግንባታ ዙሪያ ለመወያየት የኒውክሌር ሶሳይቲ ኦፍ ኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶ/ር እምሻው ዳምጠውን እና የኮይሻ ሀይድሮፓወር ፕሮጀክት ምክትል ኃላፊ ኢንጂነር አባይነህ ጌትነትን ጋብዟቸዋል።
ሙሉ ፕሮግራሙን ያዳምጡ: 


More episodes of the podcast Sovereignty Sources