''አዲስ የዓለም መልክ'': - የአፍሪካ የመደመጥ አቅም በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት

17/09/2025 1h 0min Temporada 1 Episodio 41
''አዲስ የዓለም መልክ'': - የአፍሪካ የመደመጥ አቅም በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት

Listen "''አዲስ የዓለም መልክ'': - የአፍሪካ የመደመጥ አቅም በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ም/ቤት"

Episode Synopsis

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴረዝ የፀጥታው ምክርቤትን ማሻሻል ሙሉ ስሜት የሚሰጥ (አሳማኝ) ነገር ነው ሲሉ ተናግረዋል ፡፡ ይህ ለአፍሪካ ምን ማለት ነው ?

'' አፍሪካን የሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ በቀጥታ ድምጿን ማሰማት ትችላለች። የሚጎዳቸው ከሆነ ማገድ ይችላሉ፣ የሚጠቅማቸው ከሆነ ደግሞ ማስተላለፍ ይችላሉ '' - ጃራ ሳሙኤል ቱራ በአርሲ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ክፍል መምህር
የትምህርት ክፍሉ ዲንና መምህር አበራ ለሚ በበኩላቸው፡-
''[አፍሪካ] ቋሚ መቀመጫ ማግኘቷ ከምጣኔ ሀብት አኳያ ካየነው የተለያዩ ኢንቨስትመንቶችን በመሣብ ከሌሎች ዓለማት ጋር ያላትን ዲፕሎማሲ ለማጠናከር ይረዳታል '' ሲሉ ተናግረዋል።
🎙የአፍሪካ ሀገራት በዓለም አቀፍ መድረክ በይበልጥ መሰማት ስለሚችሉባቸው አግባቦች፣ እንዲሁም 80ኛ ዓመት ምስረታውን የሚያከብረው ድርጅቱ የተጣለበትን አደራ መወጣት እንዲችል በምን ዓይነት ሁኔታዎ ከፍተኛ ማሻሻያ ሊያደርግ ይገባል በሚሉ ጉዳዮች የሶቨርኒቲ ሶርስስ ፕሮግራም አቅራቢው በአርሲ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ክፍል ዲን የሆኑት አበራ ለሚና የትምህርት ክፍሉ መምህር ጃራ ሳሙኤል ቱራን ጋብዟቸው በጥልቀት አወያይቷቸዋል።
🔊 ሙሉ ፕሮግራሙን ያዳምጡ:




More episodes of the podcast Sovereignty Sources